Who We Are

Follow us on Facebook, YouTube, Twitter: @ethiopiawinnet

Ethiopiawinnet is an independent, international civil society organization (CSO) for the promotion and defence of citizen rights for all Ethiopians. Its vision is spelled out in the “Citizens Charter for a Democratic Ethiopia,” which is the basis for all the activities and engagements of the organization. The mission of Ethiopiawinnet is the defense and advancement of the universally recognized human, civil, and political rights of the citizens of Ethiopia.

A Roadmap for a systemic political overhaul in Ethiopia

The Congress of Ethiopian Civic Associations (CECA) proudly announces the public release of our yearlong study of the modalities of “systemic” political transition in Ethiopia, entitled“A Citizen-Centered Roadmap for Systemic Political Transition in Ethiopia.”

Read the press release and Roadmap

Register for the webinar

ኢትዮጵያዊነት የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 28 ቀን 2023 ዓም በሚካሄደው የመጨረሻው ዌቢናር ክፍል፣ ከከነዚህ የሀሰት ትርክቶች ምን እንማራለን፤ ከአገራዊ ቀውስ እንዴት መውጣት ይቻላል?  ምንስ ማድረግ አለብን? በሚል መፍትሄ ላይ ያተኮረ ውይይት በምሁራንና ታዳሚዎች  ይደረጋል። 

በውይይቱም፤ 1) የሕገ መንግሥት ለውጥ ማድረግ፤ 2) የትምህርት ሥርዓቱ፤ ትምህርት ቤቶችና የከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች በየደረጃው በመፍትሄነት ሊጫወቱ በሚችሉት ሚና፣  ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ተጨማሪ አንድ ብሔራዊ ቋንቋና አንድ ወይም ሁለት ብዙ ሕዝብ የሚናገርባቸው ቋንቋዎች እንዲማሩ ማድረግ፣  ዘር ተኮር ጥላቻን በማስወገድና የአገር አንድነትን ለማጠናከር ትምህርት ስለሚኖረው አዎንታዊ ሚና፤ 3) የጂኦግራፊንና የልማትን መርህ መሠረት ያደረገ፣ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን የሚያረጋግጥ አስተዳደር፣ ካንድ ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሊያካትት በሚችል የሚዘረጋ አስተዳደራዊ አወቃቀር፤ በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የአስተዳደር ሥርዓት በክልልና ክልል መካከል የሚያስከትለውን የወሰንና የይገባኛል የጠብ ምክንያቶችን የማስወገድና የመቀነስ እንዲሁም የጋራ ሥነ ልቦናን በማዳበር የሚኖረው ሚና፤ 4) ሀገር በቀል ባሕላዊ ዕውቀቶች፣ ሽምግልና፤ ሃይማኖታዊ ተቋሞች ወይም ዘመናዊ ሲቪክ ድርጅቶች ለገር ግንባታ በሚያበረክቱት አዎንታዊ ተግባር ይህንን የዘር ጥላቻና ክፍፍል ለማቀዝቀዝ የሚኖራቸውን ሚና የዳሰሰ ውይይት ይካሄዳል። 

 እርስዎም የእነዚህ ዌቢናሮች ታዳሚ እንዲሆኑ በአክብሮት እየጋበዝን፤ ይህን ሊንክ በመክፈት ይመዝገቡ

https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_TXdo1-akSJmMRGUEFykW5g



Register for a Webinar

ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ? ይህ በውጭ ሃይሎች የተቀነቀነው የተሳሳተ ትርክት በሀገር በቀል ሃይሎች ተግባራዊ ሊሆን እንዴት ቻለ?

Date & Time: Oct 14, 2023 09:00 AM in Central Time (US and Canada)

Description:

ፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ትርክቶች መንሳኤዎች፣ የውጭና አገር-በቀል አቀንቃኞች ሚና፣ ያስከተሏቸው መዘዞችና መፍትሔዎቻችው፣

የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ "የአማራን ሕዝብ በጨቋኝነት የመሳል የሃሰት ትረካዎች ምንጭ፣ የውጪና የውስጥ አቀንቃኞች ሚና፤ የሃሰት ትረካው ያስከተሏቸው መዘዞችና ፤ ከነዚህ ምን እንማራለን፤ እንዳይደገምስ ምን የመፍትሄ ሃሣብ እናቀርባለን" በሚሉ ርዕሶች፣ በሦስት ተከታታይ ዌቢናሮች እንደሚያቀርብ በታላቅ ደስታ እየገለፀ፤ በመመዝገብ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ይጠይቃል።

የአማራና አማርኛ-ተናጋሪ የሆነውን ማሕበረሰብ አሁን የገጠመው ቀውስ እንዲሁም በሃገሪቱ ላይ በሰፊው ሰፍኖ ሕዝቡን ለማያባራ ችግር የዳረገው፤ ለረጅም ጊዜ የዘለቁት የሃሰት ትርክቶች ከየት እንደመንጩ የግንዛቤ ስምምነት አለ። እነዚህ የሃሰት ትረካዎች መጀመሪያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በቅኝ ገዢዎች የተቀነቀኑ ሲሆን፤ ዓላማውም የኢትዮጵያንና የአማራን ሕዝብ አይበገሬነትና ለነጻነቱ ቀናኤነት ገንዘቡ ያደረገውን ማንነት ለማንኳሰስና ለማሳነስ የተቃጣ ነበር።

በቀጣይ የሃሰት ትርክቱ፤ ከ1950ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀና በተለይም፤ በአንዳንድ ግራ-ዘመምና ጎሰኝነትን በሚያራምዱ ነገር ግን ራሳቸውን ለሥልጣን ተረካቢነት እጩ ያደረጉ ልሂቃንን ጨምሮ በተለያዩ ተዋናዮች ሲገፋ ቆይቷል።

የአማራ ሕዝብ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በተከታታይ በተነሱ መንግስታት ከባድ አገዛዝ ሥር የየተጨቆን አማራ የኢትዮጵያ የሕዝብ ጠላት እንደሆነ የተገፋው የሃሰት ትርክት ለከባድ አደጋ ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ትረካ እንደ EPLF, TPLF, እና OLF የመሳሰሉ አገር-በቀል የጎሳ ነፃ አውጭና ነጻነት እንቅስቃሴዎች መጀመሪያ ላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ፣ በኋላም የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት ተጠቅመውበታል።

የሀሰት ትርክቱ ምንጭ በውጭ አገርም የተገፋ ቢሆንም፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መዘዝ አስከትሏል። የትርክቱ አራማጆች በአንፃሩ የፖለቲካ ግባቸውን ሲያሳኩ፤ የአማራ ሕዝብ ግን ለግድያ፤ ለመፈናቀል፣ ቀየው ለማያባራ የአመጽና፤ የንብረት ውድመት ዒላማ ሆኖ ቀጥሏል።

የእነዚህን የሀሰት ትርክቶች ምንጮችና በአማራ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ መዘዞች በጥናታዊ-ምርምር ለመረዳት፣ ለማጋለጥና ለሰፊው ማሕበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ በቅዳሜ ኦክቶበር 14፣ በኦክቶበር 21 እና በኦክቶበር 28 ፣ 2023 ባሉት ሶስት ተከታታይ ቅዳሜዎች በሦስት የአስተምርሆት ፕሮግራም ይቀርባል ።

ዌቢናር 1 የታሪክ አመጣጥ እና መንስኤዎች ጥቅምት 14 ቀን 2023 ዓ.ም በዚህ ተከታታይ ርዕስ የሐሰት ትርክቱ ታሪካዊ መነሻ፣ ከቅኝ ግዛት ኃይሎች ጋር ያለውን ግንኙነትና የዓድዋ ጦርነትን እንመርምራለን። እንደ EPLF፣ TPLF እና OLF ያሉ የነጻነት እንቅስቃሴዎች አማሮችን ጨቋኞች አድርገው በማጥቃት እና ተከታዮቻቸውን ለማሰባሰብ የተጫወቱትን ሚናም እንቃኛለን።

ዌቢናር 2 ያስከተለው መዘዝና እና ጉዳቶች ጥቅምት 21 ቀን, 2023 ዓ.ም በዚህ ተከታታይ ርዕስ በዘለቄታው የሃሰት ትርክቶች ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአማራ ሕዝብ የደረሰባቸውን አውዳሚ መዘዝና የማይሰላ ጉዳት ይመረመራል።

ዌቢናር 3 ከዚህ ምን እንማራለን እና የመፍትሄ ሃሣቦች ጥቅምት 28, ቀን 2023 ዓም የመጨረሻው ተከታታይ ርዕሳችን በመፍትሔ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን የሚካፈሉ አራት ታዋቂ ባለሙያዎችን ያቀርባል።

Register for the webinar

Major Broadcast Media Outlets are Invited, and the Sessions will be Live Streamed on Social Media as well as Major Public and Private TV Networks: Facebook, YouTube

 



Conference on:

አማርኛ በቴክኖሎጂ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፥ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጥንታዊ ስራዎች

Amharic in Technology & Artificial Intelligence, and Ancient Works of Ethiopian Scholar

ቀን፦ መጋቢት 23: 2015 ከምሽቱ 11:00 ሰዓት እዚህ ይመዝገቡ

Date: April 01, 2023 Time: 10:00AM (Eastern Standard Time ) Register: HERE



Conference on Ethiopic Script:

ግዕዝ ፊደል፥ የብሔራዊ ማንነት ምልክትና ቀልጣፋ የአጻጻፍ ሥርዓት

Ethiopic Script: A Symbol of National Identity and Most Efficient Writing System

ቀን፦ መጋቢት 02: 2015       ከምሽቱ፦ 12:00 ሰዓት             እዚህ መዝገቡ

Date:  March 11, 2023               Time:  10:00AM  (Eastern Standard Time  )         Register: HERE   

Watch on Facebook

Watch on YouTube

                          

 

You are cordially invited by Ethiopiawinnet to be a part of this conference addressing the 

'State of Ethio-American Relations: Challenges and Opportunities".

 Please attend, cover or live stream the webinar.  Please also help us announce the webinar.

 Date: January 21, 2023

          ቅዳሜ ፣ ጥር 13  2015

Time:  10:00 AM Eastern Standard Time

            በኢትዮዽያ የሰዓት አቆጣጠር ፥ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ

Registration link: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_D4_zwQ3pRZOlVgikO8ieTQ

'State of Ethio-American Relations: Challenges and Opportunities".

Previous Ethiopiawinnet’s Events


Ethiopiawinnet Conference (Webinar)

Oct 15, 2022, starting at 9:00 AM. Please register ONLY ONCE so others get the chance to participate. You'll receive a unique registration confirmation for you to use on conference day.

To register for the webinar click here

Watch the webinar Part I on YouTube

Watch the webinar Part II on YouTube

Watch the webinar on Facebook

For detail webinar schedule click here.

For detail webinar schedule click here.

Embed Block
Add an embed URL or code. Learn more

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት/ጉባኤን በኢትዮጵያ ዉስጥ ለማስተዋወቅ የሚዲያ ሽፋን

በአዲስ አበባ በኢትዮጵያዊነት መክፈቻ ላይ ወጣት የኪነት ቡድን ያቀረቡት ሙዚቃ

የፕረስ ኮንፈረንስ

በአሻም ቲቪ https://youtu.be/_OTZOAIzR-Y

የዶ/ር እርቁ ይመር ቃለመጠይቅ በአሻም ቴለቪዥን https://www.youtube.com/watch?v=F7qjzZI_UOw

በሸገር ሬድዮ የካቲት 29፣ 2014- በዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተው ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ማህበር አዲስ አበባ መምጣቱ ተነገረ by ሸገር 102.1FM(ShegerFM) | Mixcloud

ቪኦኤ ራዲዮ  https://amharic.voanews.com/live/audio/68/6460158#:~:text=media%20source%20currently-,available,-55%3A17

በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ

ፐራይም ሚድያ

በመረጃ.ኮም ላይ

https://mereja.com/amharic/v2/686692

ከኢፌድሪ ፕሬዝዳን ጋር የነበረንን ውይይት ተከትሎ የተሰሩ ዜናዎች

በፕሬዝዳን ቢሮ ትዊተር https://twitter.com/POEthiopia/status/1504649918719438864

በፕሬዝዳንት ፌስ ቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/photo.php?fbid=335976285228294&set=pb.100064477764605.-2207520000..&type=3

የማስተዋወቂያ መድረክ ሽፋን

ዜና በHarmony Tube (ሀርመኒ) - https://youtu.be/DsdQhkEXMAs

ቀጥታ ስርጨት በፌስቡክና ዙም(በድርጅታችን አማካንነት)፡ https://fb.watch/c6FJrX6xAo/

ዶ/ር እርቁ የሃገራዊ ምክክር ላይ ከኢ.ዜ.አ ጋር የነበራቸው ፓናል ውይይት በኢሳት ዜና ላይ ፡ ከ18፡50 እስከ 20፡11 ደቂቃ ድረስ  Ethiopia - ESAT Amharic News Wed 23 Mar 2022 - YouTube

ሌሎች

የድርጅታችን የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተስፋሚካኤል መኮንን ከየኔታ ትዩብ ጋር የነበራቸውን ቆይታ  https://youtu.be/j9Jd03NqngE

ዶ/ር እርቁ ከኢ.ፕ.ድ (አዲስ ዘመን )ጋር የነበራቸው ቆይታ፡ https://www.press.et/ama/?p=68723&fbclid=IwAR17kz-ITjnsqEttM1wNXnc2lkNhNIqkO6aqjXH_O0Z74Ih36PuNONNAaWI

ከሃገራዊ ምክክር ሥራው ላይ የኢትዮጵያዊነት ጉዳይ አጀንዳ መሆን እነዳበት

https://ethiopianreporter.com/index.php/article/24898

የኢትዮ ኤፍ ኤም 108.7 ከአቶ ተስፋ እና አቶ ሞገስ ጋር ዘወትር ሰኞ የእኛ ጉዳይ ከሚለው የሬድዮፕሮግራም ላይ ቀርበው የነበራቸው የቀጥታ ሥርጭት ዝግጅት በኋላ የተሰራው ዜና

https://ethiofm107.com/2022/03/22/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8a%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%aa%e1%8a%a9%e1%88%88%e1%88%9d/

ግፈኝነት ይብቃ!

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

በጎ አመለካከት ያላቸው ሀገሮችና የዓለምሕዝብ፣ ከታሪካዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ እንጠይቃለን። በዚህ የዘር ጥላቻ ጦርነት በሚሊዮን የምቆጠሩ አማራዎችና አፋሮች ከቀያቸው ተሰደው በከፍተኛ ችግር ስለሚገኙ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎች በያይነቱ እንዲደርሳቸው ፣ በውጭም በውስጥም ያሉ የረዲኤት ድርጅቶችና የኢትዮጵያ ሕዝብ ርብርብ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡ ሙሉዉን መግለጫ ያንብቡ

ቀና በል (በቴዲ አፍሮ)

ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራው

የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው፤

ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት

ማንም አይገታው የተነሳለት፣

ለታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር የተዘጋጀ መታሰቢያ

Celebrating the Life & Career of a Distinguished Ethiopian Scholar

Date: Oct. 9, 2021 Time: 10:00AM — 1:00PM Eastern time

See the details

Please use this youtube link to watch the event live: https://www.youtube.com/watch?v=jmegVmI6VLc


 

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

የሀዘን መግለጫ

ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ/ም

 በታላቁ ምሁር በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ህልፈተ ሕይወት የተስማንን ጥልቅ ሀዘን በራሳችንና በመላው የኢትዮጵያዊነት ድርጅት አባሎቻችን ስም እንገልፃለን።  ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።

ፕሮፌሰር ጌታቸው  ኃይሌ  ከዘጠኝ ዓመታት  በፊት ድርጅታችንን ከመሠረቱት ጥቂት ግለሰቦች መሀከል አንደኛውና ዋነኛው ሲሆኑ፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ንቁ ተሳታፊና ድርጅታችንን በሀሳብ፤ በገንዘብና በፅሁፍ ሲረዱን ከቆዩት መካከል ናቸው። ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው በኢትዮጵያ ታሪካና ሥነ ጽሁፍ ዕውቀት፡ ችሎታቸውና ተመራማሪነታቸው በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ከፍትኛ ቃዋቂነትን ያተረፉ ታላቅ ሰው ነበሩ። ለዚህም ከተለያዩ ድርጅቶችና መንግሥታት የበጎ ሥራዎች ሽልማትና የዕውቅና ማዕረጎችን ከከፍተኛ ክብር ጋር አግኝተዋል። እ ኤ አ በ1988 ከአሜሪካን መንግሥት የተበረከተላቸው የማካርተር  የበሳል አእምሮና ምጡቅ ተመራማሪ ሽልማት በመስኩ የመጀመሪያው ተሸላሚ አድርጎ አቸዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ደከመኝ ስለቸኝ ሳይሉ በዘመናቸው በተለይም ከኢትዮጵያ ታሪክ ቅርስ፣ ባህልና ሃይማኖት ጋር   የተያያዙ በርካታ መፃህፍት ፣ የምርምርና የጥናት ፅሁፎችን አበርክተዋል። አብዛኞቹም በአማዞን ድረገፅ በኩል የሚታደሉ  ናቸው።

ሀገራችን ዛሬ አንጋፋ ልጅዋን አጥታለች። ለሁላችንም እግዚአብሔር  መፅናናቱን እንዲስጠን እየጠየቅን፤ የእሳቸውንም ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን እንለምናለን።

 

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

የሥራ አመራር ቦርድ

On April 17, 2021, Ethiopiawinnet organized an international virtual conference on:

The Ramifications of Western Reactions to the Current Crises in Ethiopia

Ethiopiawinnet is immensely grateful to the panelists, moderators and organizing committee for their outstanding contributions. We would also like to thank those who attended the live webinar.

We have received a number of requests to share the recorded webinar.

Here is the link to the recorded webinar:  https://www.youtube.com/watch?v=EspideQZm1U

Please share it with your networks.

To make your navigation of the long video easier, the video is broken into chapters/ segments by session and speakers.  You can see the chapters under the description of the video. By clicking the timestamp, you can view the specific speech.


Urgent Appeal to the UN Security Council (Read the statement)

by:

Ethiopian Dialogue Forum (EDF)

Ethiopian Borders Affairs Committee (EBAC)

Ethiopiawinet-Council for the Defense of Citizens Rights

Vision Ethiopia







January 27, 2021

 ውድ ወገኖቻችን፤

 Ethiopian Affairs በሚል ስም “ጉዳዩ:- የኢትዮጵያን ኅልውና አደጋ ላይ የጣሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ስልጣናቸዉን ይልቀቁ!!” የሚል ርዕስ  ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ በሀገራችን ጉዳይ ላይ ያተኮረ መግለጫ በሶሻል ሚዲያ ተበትኖ ተመልክተናል።

 ድርጅታችን በአጭሩ ሲጠራ “ኢትዮጵያዊነት” በሙሉ ስሙ ሲጠራ

 “ኢትዮጵያዊነት፦ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ” በእንግሊዘኛው አጠራር ደግሞ “Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights”  በመግለጫው ከተጠቀሰው “ኢትዮጵያዊነት--(ሰሜን አሜሪካ)” የሚባል ድርጅት ጋር ምንም ግኑኝነት የለዉም።  ይህንንም ስሙ የተጠቀሰ ድርጅትም ሆነ ግለስብ የማናውቀውና የማይመለከተን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ሥራ አመራር ኮሚቴ

ኢትዮጵያዊነት፦ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights

December 18, 2020

የሀዘን መግለጫ

ታህሳስ 8፣ 2013

ለአቶ እያሱ በካፋ ቤተሰቦች፤ ጓደኞችና ወዳጆች በሙሉ

በያሉበት

አቶ እያሱ በካፋን አብዛኞቻችን ያወቅናቸው ድርጅታችን ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ በህገር ቤት ለሚያካሂደው እንቅስቃሴ በበላይነት እንዲመሩ ታስቦ ከአንድ ወር በፊት ክተቀላቀሉን በህዋላ ነው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ባሳዩን የሀገርና የሥራ ወዳድነት ባህሪይ፤ ተግባቢነትና አርቆ አስተዋይነት ለምንጊዜውም በልባችን ተቀርጾ ይኖራል፡፡

ድርጅታችን ብሎም ውድ ሀገራችን በጣም ትልቅ ስዉ እንዳጣችም ይሰማናል፡ በህልፈታቸው ምክንያት የተስማንን ጥልቅ ሀዘን በመላው አባሎቻችን ስም እየገለጽን ለመላው ቤተስባቸውና ጓደኞቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን አምላካችንን እንለምናለን፡

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

የሥራ አመራር ኮሚቴ

November 12, 2020

በትግራይ ክልል ሕግን ለማስከበር እየተወሰደ ስላለው እርምጃ ፣

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

አሁን በትግራይ ክልል አመራሮች ላይ የሚካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በጥሞናና በጥንቃቄ እንዲከናወን፣

·      መንግሥት ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ በሚያደርገው ዘመቻ ሰላማዊ ሕዝቡ እንዳይጎዳ እስካሁን እያደረገ ያለውን ጥንቃቄ እያደነቅን ለወደፊቱም በዚሁ እንዲቀጥል እናበረታታለን፡፡

·       አንደኛው የችግሩ ምንጭ በየክልሉ የተዋቀረው አላስፈላጊ ‘ልዩ ኅይል’ መሆኑ ታውቆ  የየክልሉ  "ልዩ ኃይሎች"  ከመክላከያ ሠራዊትና ከፌደራል ፖሊስ ውስጥ እንዲጠቃለሉ የሚያስችል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲወሰድ እናሳስባለን፡፡

·      የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌወች፣ አባገዳዎች፣ የሲቪል ማኅበራትና የሜድያ ኃላፊዎች  ሁሉም ለሰላምና ለሕግ መክበር ተከታዮቻቸውን እንዲያስተምሩ አጥብቀን  እናሳስባለን፡፡

·      በኅብረተስባችን መሀከል እስከአሁን የመከፋፈል፤ የእርስ በርስ ጦርነትና ጥላቻን በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፋ የሚያደርገው በሌሎች ሀገሮች ታይቶ የማይታወቀው በህወሃት፤ በዚሁ ወንጀለኛ ቡድን፤ የተቀነባበረው ዘርና ቋንቋን መሠረት ያደረገ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲታረም ወይም በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በነፃነቷና ባንድነቷ ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

ሙሉዉን መግለጫ ያንብቡ

በአማራና አናሳ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈጸም ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ጥቃት በአስቸኳይ መቆም አለበት

ኢትዮጵያዊነት፦የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤከ የተሰጠ መግለጫ September 20, 2020

ለወደፊቱ በአማራውና በአነስተኛ የህብርተስቡ ክፍሎች ላይ በማንነታቸው ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ ጥቃትና  እልቂት ከመድረሱ በፊት፤          

1.                 የፌደራሉ መንግሥት በሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙት የአማራና መተከል አመራሮች፣ በተደጋጋሚ ለሰው ህይወት መጥፋትም ሆነ ለንብረት መውደም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተጠያቂዎች መሆናቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፤

2.                 መንግሥት የጥፋቱ ተሳታፊዎችን አሳዶና ተከታትሎ በመያዝ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንዲያደርግ፤

3.                 መንግሥት ለወደፊቱም እንዲህ ዓይነቱ የዘር ማጥፋቱ ተግባር እንዳይፈጸም የሚያግድ የህግና የድርጅታዊ  ዝግጅት እንዲዲያደርግ፤

4.                 መንግሥት ለተጎዱት ወገኖች አስፈላጊውን ካሳ እንዲከፈሉ እንዲያደርግ

5.                 በተደጋጋሚ የጥፋቱ ስለባ የሆኑት የህብረተሰቡ ከፍሎች ለወደፊቱ ከተመሳሳይ ጥቃት እራሳቸውን የሚክላከሉበት ዘዴ እንዲያመቻቹና ለዚሁም የፌደራሉና የመተከል አስተዳደር ሁኔታዎችን እንዲፈቅዱና እንዲያመቻቹላቸው እናሳስባለን፡፡

ሙሉዉን መግለጫ ያንብቡ











በኦሮምያ በቅርቡ ስለተከሰተው የኅይማኖትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ኢትዮጵያዊነት ያወጣዉ መግለጫ











Ethiopiawinet:-Council for the Defense of Citizen Rights sent a letter to President Donald Trump on Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) negotiations.

Considering long term, historic and mutually beneficial relations between the peoples and governments of the United States of America and Ethiopia, we earnestly request that:

1) The US should restore its neutral status to the ongoing talks between Ethiopia, Egypt, and the Sudan.

2) Henceforth desist from issuing undue pressure on Ethiopia

3) Assign experienced diplomats and professionals to observing future talks to manage its participation in such complex and critical regional negotiations.

4) Make efforts to clarify to the Ethiopian public that its relations with Ethiopia is as important as those in Egypt and the Sudan and intends to remain engaged without taking sides.

Please read the full letter.

         ከኮሮና ቫይረስ አስጊ የወረርሺኝ ደዌ እራስን ቤተሰብን የሥራ ባልደረባንና አገርን ማትረፍ

                                     ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

የኮሮና በሽታ ገብቷል ወይንም እየተንሰራፋ ነው በተባለበት አጥቢያ ያሉ አዛውንትና ቀድሞውንም ሌሎች የተለያዩ ደዌዎች ጥቃት ያደረሱባቸው ሰዎች ሁሉ ከቤት ሳይወጡ በጤንነት ያሉ ወጣትና ጤናማ ዘመዶች ሊረዷቸው ይገባል።

1.      ጉንፋን መሰል ሕመም በተለይ ከትኩሳት ጋር የያዛቸው በማንኛውም ዕድሜ  ያሉ ሁሉ እቤት በመቆየት ሁኔታቸውን ያዳምጡ፡ ውሎ ካደረ ወይም የመተንፈስ ችግር ከጀመረ ደግሞ ቢቻል የጤና ባለሙያ አነጋግሮ እርዳታ መሻት፣ ባይቻል አፍና አፍንጫን በማስክ ወይም በሻርፕ ከሸፈኑ በኋላ እጅን ሙልጭ አድርጎ በሳሙና ታጥቦ ወደ ሐኪም መሄድ ይገባል፡፡

2.     ማንኛውም ሰው እጅን በሳሙና ሁልጊዜ አገላብጦ እሽት አድርጎ በመታጠብ፤ ጎጂ ተውሳክን ለማስወገድ ይቻላል። እጅን በውሃ አርሶ መተው ወይም በቅጡ አለመታጠብ ቫይረሱን ሌሎችንም ጎጂ የማይታዩ ህዋሳትን ሊያስወግድ ስለማይችል፤  እጅ ደግሞ ከፊት ካፍንጫ ካይን መነካካት ስለማይወገድ፤ ቫይረሱ ከጅ ወደሰውነት የመግባት ዕድል እንዳያገኝ መፍትሄው  እጅን እሽት አድርጎ መታጠብ ነው።

3.     ባልታጠበ እጅ ፊትን አፍንጫን ዓይንን አፍን መነካካት ማቆምን ልማድ እናድርግ። ከቤት የመውጣት የማይቀርበት ጉዳይ ካጋጠመ እስካርፍም ባይገኝ በተደራረበ ያንገት ልብስ ወይም ንጹህ ጨርቅ አፍና አፍንጫን ጠበቅ አድርጎ በማሰር ሸፍኖ መሔዱ በመጠኑ ቫይረሱ እንድይገባ ይበልጡኑ እኛ ይዘነው ከሆነ እንዳናስተላልፍ ጠቃሚ መሆኑ ተደርሶበታል።   

4.     ሁላችንም ከሌላ ሰው በምንገናኝበት ጊዜ ራቅ ብለን በማጎንበስ ሰላምታ መለዋወጥን እንምረጥ፡ እጅ አለመጨባበጥን  አለመተቃቀፍን፣ አለመሳሳምን አጥብቀን በተግባር እናዉላቸዉ፡፡ ይህን አጥቂ ጠላት በኩርፊያም ይሁን በጡጫ እስክናስወግድ እነዚህን የመቀራረብ ባህሎቻችንን ተወት እናድርጋቸው።

5.     ሳልና፣ ማስነጠስ መናፈጥ ሲያስገድዱ ወይም ሲታሰቡ  ዞር ብሎ አፍና አፍንጫን በክንድ መሐል አፍኖ መሳል፣ ወይም በወረቀት መሀረብ አፈን አድርጎ ከማይነካካ፣ ልጆችም ከማይደርሱበት ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣል ።

6.     በጅ የሚነካኩ እቃዎችን መሳሪያዎችን መጠቀሚያዎችን በአልኮል ወይም ሳኒታይዘር መጥረግ፡፡ እነዚህ እቃዎች በማይገኙበትም ስፍራዎች በተቻለ መጠን ባለው ሳሙና ሳያነካኩ ባንድ አቅጣጫ መጥርግና ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡

7.     እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ሰው ተበራክቶ ከሚገኝበት አለመሔድ። በተለይም ወረርሽኙ ጠፋ እስካልተባለ ድረስ መጠጥና ዳንስ ሰርግና ጭፈራ ቤቶች የበለጠ ለቫይረሱ መተላለፍ ምቹ ስለሚሆኑ አይሂዱ። የሺሻና የጫት ቤቶችም እንዲሁ ከራሳቸው የጤና ችግር ሌላ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ስለሚሆኑ ቫይረሱም የተበራከተ ሊሆን ይችላል። መንግሥት ወይም የክፍለሀገሩ የጤና ድርጅትና አስተዳደር የሚያወጡትን የጤና አጠባበቅና ያለመሰባሰብ ሕጎች ተከታትሎ በተግባር ማዋል።       

8.     በቂ ፈሳሽ መጠጣት ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ነጭ ሽንኩርት መመገብ ደዌውን ያስወግዳል ባይባልም ለመቋቋም ብርታት ይጨምራል።

9.     በየጊዜው የከፋ ተላላፊ በሽታ ገለጻ ምክርና እውቅናን እያነበቡና እያዳመጡ ሕጋዊ የጤና መምሪያ የሚሰጠውን በመከታተል ፈጣሪያችን ልንከላከለው ከምንችለው በድጋፉ፤ ልንከላከለው ከማንችለው በጸጋው  ይጠብቀን:: አሜን

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

POSTER1.PNG

To see full-size poster click here. Please share it.

ኮሮና ቫይረስን ለመቋቋም መፍትሔዎችን ሁሉ በተግባር እንፈጽም

በመላው ዓለምና በሐገራችንም የተከሰተውን ለሕይወት ጠንቅ የሆነውን ኖቬል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ለመቋቋም ከመንግሥት፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከጤና ድርጅቶችና ባለሙያዎች፤ ግል ድርጅቶችና ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የጀመሯቸው ሕዝብን ስለበሽታው መንስኤና አመጣጥ የማሳወቅ፤ ራስን ከመንስኤው ስለማግለል፤ ስለመመርመር፤ የሕክምና ዕርዳታ ስለማግኘት፤ እና ከበሽታው አለመያዝ በሃኪም ማረጋገጫ ከተገኘም በኋላ ክትትል ስለማድረግ የማስተማርና የበሽታው ጠንቅ (ቫይረሱ) በሰፊው እንዳይሰራጭ ለመግታት የሚደረገው ጥረት ሁሉ ለሕዝብ ደህንነት የሚደረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች በጣም የበለጸጉ ሐገራት በሀብታቸውና ጠንካራ የጤና ተቋሞቻቸው ብቻ ተማምነው ሳይሆን በቅድሚያ በሳይንሳዊ ተመክሮ ላይ በተመሠረተ የመከላከል ትምህርት ሊረዱት በሚችሉት ቋንቋ በሰፊው ለሕዝብ ማቅረብና ማዳረስ ሲቻል መሆኑ እሙን ነው።

ከወረርሽኙ ለመከላከል ከሚጠቀሱት ዘዴዎች ውስጥ ፊትን አለመነካካት፤ በተቻለ መጠን በመደጋገም እጅን መታጠብ፤ በሽታው የተጠናወተን መሆኑን ካወቅን ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ማራቅ፤ ስለ ሕመሙ ሰፊ ግንዛቤ እንዲገኝ ማድረግ እንዲሁም ሕክምና የሚገኝበትን ሥፍራ ማሳወቅ ይገኙበታል፡፡

ማሕበራዊ ባህላዊ ሠላምታ በርቀት (ሶሻል ርቀት; ሶሻል ዲስታንስ) የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ መፍትሔ ነው!

ማሕበራዊ ሠላምታችንን በርቀት መተግበር አብሮነታችንን አያሳንስም!

ሕይወትን ለማትረፍ ቅድሚያ እንስጥ!

ሙሉዉን መግለጫ ያንብቡ ይህን ይጫኑ

PRESS RELEASE ON GERD TALKS: ETHIOPIA’S RIGHTS OVER ITS NILE WATER SHOULD BE RESPECTED BY ALL

Ethiopiawinnet expresses its appreciation for the peaceful initiative and efforts taken by the tripartite countries (Ethiopia, Egypt and the Sudan) and the observer role played by the US, IMF and the World Bank to help expedite negotiations to resolve issues regarding the GERD and the ultimate utilization of the Nile River resources in a mutually beneficial and equitable manner.  It is, however, incumbent upon us as concerned citizens, as we express our optimism of the positive outcome of these negotiations to underline the need for ensuring that Ethiopia’s basic rights for the use of Nile waters are also duly respected and protected. 

Among the concerns that have been noted by Ethiopiawinnet as serious challenges in these negotiations under the current circumstances, mention should be made of the following:

 1)      Rushed Negotiations: Given Ethiopia’s good faith agreement with its’ tripartite partners

(Egypt and the Sudan) for equitable and mutually beneficial use of the Nile waters, and it’s acceptance of observing partners (US, IMF and the World Bank), these negotiations are taking place in a very rushed pace, not taking into considerations the findings of the joint GERD technical team, and considerations of affording adequate time for the parties to inform & discuss with their public and respective parliaments.  

2)      Lopsided ‘Equitable’ Use of Nile Water in These Negotiations: - The UN water and watercourse convention has put in place the principles of Equitable and Reasonable Utilization of the Nile waters https://www.unwatercoursesconvention.org/documents/UNWC-Fact-Sheet-4-Equitable-and-Reasonable-Utilisation.pdf to conclude a durable agreement in such negotiations. It appears in these rushed and politicized negotiations, the question of Ethiopia’s sovereign right for equitable use of the Nile Waters is taken for granted to placate Egypt and sideline weak Ethiopia to accept these terms.  Additionally, an agreement of such magnitude should take into consideration the interests of the current and coming generations. Disputes on Nile River should therefore be carefully mediated in a way not to compromise the rights of future generations living in the basin.

 It is obvious that an attempt is being made by Egypt and its supporters to demand an undiminished water supply by Ethiopia without taking into account the fact that Ethiopia has the sovereign right and need to utilize its natural water resources for its current population of over 110 million which is expected to increase to 172 million by 2050. 

3)      Politicization of GERD discussions: The Nile Basin Initiative (NBI) to establish legal frameworks and institutions by the upper and lower riparian states, based on internationally accepted norms, has been challenged by Egypt repeatedly, due to its unfortunate politicization and securitization of the river shared by 11 riparian countries. The Nile question would have been answered on its entirety had all basin countries committed to the Cooperative Framework Agreement (CFA). Egypt chose not to cooperate. This is unprecedented in any water treaty negotiations anywhere in the world. The following are additional reasons that hamper Nile negotiations: 

Read the full press release.

PETITION REGARDING THE GRAND ETHIOPIAN RENAISSANCE DAM (GERD)

Professionals of Ethiopian origin in the Diaspora have filed this petition to:

(1)    The Secretary General of the United Nations, to exert influence against Egypt’s unacceptable behavior and avert potential conflict in the region;

(2)    The President of the Pan African Parliament, to support the Nile Basin Initiative and to demand Egypt to refrain from undermining Ethiopia’s sovereign rights over the sources of the Blue Nile and the dam; including but not limited to its operations.

(3)    The Chairperson of the African Union Commission, to support the Nile Basin Initiative and to demand Egypt to refrain from undermining Ethiopia’s sovereign rights over the sources of the Blue Nile and the dam, including but not limited to its operations;

(4)    The President of the United States, to be a neutral facilitator;

(5)    The President of Russia, to be a neutral facilitator;

(6)    The President of the World Bank, to use its good offices to play the role of a neutral facilitator and revisit its refusal to finance the GERD project;

(7)    The President of the Arab Republic of Egypt, to cease and desist undermining the Nile Basin Initiative, and the sovereignty of Ethiopia on the basis of a water security mindset;

(8)    The Speaker of the Arab Parliament, to retract the recent letter and to cease intimidating Ethiopia;

(9)    The Egyptian academics and professionals, to find an amicable and mutually beneficial solutions to the problem; and

(10) The Prime Minister of Ethiopia, to fight for a reasonable resolution, taking into consideration the water rights of future generations, based on a framework that does not compromise in anyway the sovereignty of the country over the sources of the Blue Nile and the dam, including but not limited to its operations. 

Read full petition.

ዘረኝነትን፣ ጎሰኝነትን እናምክን፤ ለዜግነት ክብር እንታገል!

ጥቅምት 15፣ 2012 ዓ ም

ባለፉት ጥቂት ቀናት በሀገራችን፣ በተለይም በኦሮምያ ክልል የተፈጠረው ሥርዓተ አልበኝነት እስከ 67 የሚሆኑ ወገኖቻችንን ሕይወት ቀጥፏል፣ ከ 300 ያላነሱ ቆስለዋል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት በየከተማው ወድሟል፤ ቤተ ክርስቲያን ከአደጋው ለመጠለል የገቡ ተሳደው በቦምብ ሕይወታቸውን እንዲያጡ ሆነዋል፤ ወደ ሆስፒታል ሕይወታቸውን ከደረሰባቸው ጉዳት ለማትረፍ ሲወሰዱ እንዳይሄዱ ታግደው ባሉበት እንዲገደሉ ተደርገዋል። ድርጅታችን “ኢትዮያዊነት: የዜጎች መብት ማስከበርያ ጉባዔ” የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀዘኑን ይገልፃል።

Read more


 

Ethiopiawinnet has just launched a GoFundMe campaign

Ethiopiawinnet has just launched a GoFundMe campaign to raise resources required to fund the startup costs of the Ethiopiawinnet Institute in Ethiopia.

Want to join us in making a difference? we are raising money to benefit Ethiopiawinnet Council for the Defence of Citizen Rights, and any donation will help make an impact on the establishment of an Ethiopiawinnet Institute in Ethiopia and its educational and research projects it planned to launch in Ethiopia. Thanks in advance for your contribution to this cause that means so much to us.

ttps://www.gofundme.com/f/Help-Ethiopiawinnet

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን መልሶ ለማስረጽ - የኢትዮጵያዊነት ተቋም ለማቆም ተነስተናል” - ዶ/ር ዕርቁ ይመርና አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር

We define Ethiopiawinnet as ownership and pride of the essentials of being Ethiopian. That means, the culture lived, the history accomplished the dictum and aspirations wanted.  Social responsibility for impact in Ethiopia is a shared value of Ethiopiawinnet.

The mission of Ethiopiawinnet is to foster patriotism, civic engagement and institution building to empower Ethiopians in establishing an accountable democracy.

To engage every Ethiopian in making a difference, Ethiopiawinnet invites you to learn more about our three pillars:

1. Patriotism

Evoking patriotism through education of Ethiopian history, this pillar is one we believe everyone will be able to relate to and find value in.

Learn more about Patriotism on Ethiopiawinnet

2. Civic Engagement 

The second pillar, civic engagement, for those that want to make a difference in Ethiopia, is an opportunity to develop the combination of knowledge, skills, values and motivation to make that difference.  While this pillar also entails education, a major component that differentiates it form the first pillar, Patriotism, is advocacy.  Advocacy on behalf of citizen’s rights, which Ethiopiawinnet provides council for.

Learn more about Civic Engagement on Ethiopiawinnet

3. Institution Building 

Is it better to strengthen the current institutions in Ethiopia or start over in institution building, our third pillar?  This pillar, led by Ethiopiawinnet scholars across various disciplines from the most prestigious educational institutions around the world, is one we believe will most engage politicians, professionals and administrators. The papers published by our scholars educate in and provide discourse on the current state of institutions in Ethiopia and the way forward.

Learn more about Institution Building on Ethiopiawinnet

 

Calendar Daily Digest

Calendar

4th Ethiopiawinnet Symposium

August 11-12, 2018
The Catholic University of America
Washington, DC 20064

The late Professor Taddesse Tamrat on Ethiopian Calendar and History.

Dr. Erku Yimer, Ethiopiawinnet Chairman, interviewed by Reeyot Alemu

Vision Ethiopia with PM Dr. Abiy Ahmed

ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴና ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ በኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ላይ ኢትዮጵያዊነት ሲምፖዚየም ላይ የተደረገ ዉይይት ክፍል 1

ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴና ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ በኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ላይ ኢትዮጵያዊነት ሲምፖዚየም ላይ የተደረገ ዉይይት ክፍል 2


Latest News


Press Releases